ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተካሄደ።
ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተካሄደ።
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የማኔጅመንት አባላት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂደው፣ ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ተደራሽና ዘመናዊ ለማድረግ እየተሻሻለ ያለውን የCIS ሲስተም አፈፃፀም ገምግመዋል።
በውይይቱ ተገልጋዮች ካሉበት ቦታ ሆነው ቀጠሮ ማስያዝና ቅሬታ ማቅረብ የሚያስችለው የሲስተሙ ክፍል ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን፣ የተሰጡ ግብአቶችን በማካተት በቅርቡ ሙከራ እንዲደረግበት አቅጣጫ ተቀምጧል።
ከዚህ በተጨማሪ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ብልሹ አሰራሮች ላይ ውይይት ተካሂዶ፣ የስራ ክፍል ኃላፊዎች በቀጣይ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎቻቸውን እንዲያጠናክሩ በጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም