የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በየካ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ በጉለሌ ፣ ቂርቆስ እና ልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ከቴሌ ብር ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግና ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን በኦን ላይን በ https://landleasedocument.ddlb.gov.et/ መግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነድ ግዢውን ከታህሳስ 27/2018ዓ.ም እስከ ጥር 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት መፈፀም ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበትን ስሊፕ፣መታወቂያ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በአንድ (1) ኤንቨሎፕ በማሸግ ጥር 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡